News Archive News Archive

Back

በገጠራማው የኢትዮጵያ ክፍል ለሚኖሩ ዜጎች ዘመናዊ የኢነርጂ ምንጮችና ቴክኖሎጂዎችን ተደራሽ ለማድረግ እንደሚሠራ ተገለጸ

በገጠራማው የኢትዮጵያ ክፍል ለሚኖሩ ዜጎች ዘመናዊ የኢነርጂ ምንጮችና ቴክኖሎጂዎችን ተደራሽ ለማድረግ እንደሚሠራ ተገለጸ

ጥር 6 ቀን 2013 .ም፤ አዲስ አበባ

በገጠራማው የኢትዮጵያ ክፍል ለሚኖሩ ዜጎች ዘመናዊ የኢነርጂ ምንጮችንና ቴክኖሎጂወችን ተደራሽ ለማድረግ እንደሚሠራ የውሃ፣መስኖና ኢነርጂ ሚኒስትሩ / / ስለሺ በቀለ ተናገሩ፡፡

ክቡር ሚኒስትሩ ይህን የተናገሩት ጥር 6 ቀን 2013 . የኢትዮጵያ የገጠር ኢነርጂ ልማትና ማስፋፊያ ማዕከል ዳግም ተደራጅቶ ወደ ሥራ መግባቱ በተበሰረበት መርሐ ግብር ላይ ነው፡፡

በኢትዮጵያ 80 በመቶ ከሚሆነውና በግብርና ከሚተዳደረው የህብረተሰባችን ክፍል በአብዛኛው የኤሌክትሪክ ኃይል የማያገኝ በመሆኑ ለምግብ ማብሰያና ለመብራት የማገዶ እንጨትን፣ የከብቶች ፍግንና ከከሰልን እንደሚጠቀም ገልጸው ይህን ለመቀየር ዘመናዊ የኢነርጂ ምንጮችና ቴክኖሎጂዎችን ተደራሽ ለማድረግ በማዕከሉ በኩል እንደሚሠራ ሚኒስተሩ ተናግረዋል፡፡

የኢትዮጵያ የገጠር ኢነርጂ ልማት ማስፋፊያ ማዕከል በአዋጅ 269/1994 . ተቋቁሞ በገጠር አካባቢ ያለውን የኢነርጂ አቅርቦት እያጠና የኢነርጂ ምንጮችን በማልማትና በማስፋፋት በርካታ ሥራዎችን ሢሠራ ቆይቶ በአዋጅ 691/2003 ማዕከሉ ፈርሶ ስልጣንና ተግባሩ ለውሃ፣መስኖና ኢነርጂ ሚኒስቴር፣ ለአካባቢ ደንና አየር ንብረት ለውጥ ኮሚሽን(በወቅቱ ሚኒስቴር ነበር) እና ለማዕድንና ነዳጅ ሚኒስቴር ተሰጥተው ቆይቶ ነገር ግን በአዋጅ 1097/2011 . እንደገና ተቋቁሞና የመዋቅር ጥናት ተካሂዶ በድጋሚ ተደራጅቶ ሥራውን በይፋ ጀምሯል፡፡

የኢትዮጵያ ገጠር ኢነርጂ ልማት ማስፋፊያ ማዕከል የተሻሻሉ ማገዶ ቆጣቢ የማብሰያ ምድጃዎች፣ የባዮ ጋዝ ቴክኖሎጂ፣ የሶላር ሆም ቴክኖሎጂ፣ አነስተኛ ኃይድሮ ፖወርና የባዮ ፊውል ቴክኖሎጂዎች ላይ በስፋት ይሠራል፡፡

ጉርድ ሾላ አካባቢ በሚገኘውም በማዕከሉ ወርክሾፕና ላብራቶሪ ቅጽር ግቢ ከጥር 6/2013 እስከ ጥር 8/2013 . የሚቆይ የኢነርጂ ቴክኖሎጆዎችን የሚያሳይ ዓውደ ርዕይም ተዘጋጅቶ በመታየት ላይ ይገኛል፡፡