ኢነርጂ ልማት

መንግስት የነደፈውን የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ እውን ለማድረግ አስተማማኝ የሀይል አቅርቦት መኖር ወሳኝ ነው፡፡ የኢነርጂው ዘርፍ ቀድሞ በማደግ ለኢንዱስትሪው ልማትና ለህብረተሰቡ አስፈላጊ የሆነውን ኃይል  ለማቅረብ እንዲያስችል መጠነ ሰፊ ስራዎች በመሰራት ላይ ይገኛሉ፡፡ ሀገራችን ከሌሎች ሀገራት ጋር ስናነፃፅር በኢነርጂው ዘርፍ ከፍተኛ ሀብት አላት ፡፡

ከ45,000 ሜጋ ዋት በላይ ከውሃ፣100,000 ሜጋ ዋት በላይ ከንፋስ፣5,000 ሜጋ ዋት ከጀዎተርማል የኤሌክትሪክ ሀይል ማመንጨት የሚያስችል እምቅ ሀይል ያላት ሲሆን ሌሎች የኢነርጂ አማራጮችን ሣይጨምር ከ150,000 ሜጋ ዋት በላይ የኤሌክትሪክ ሀይል ማመንጨት ያስችላል፡፡

በሚቀጥሉት አመታት ሀገራችን የሀይል አቅርቦትን በማሣደግ ለጎረቤት ሀገራት በመሸጥ የውጭ ምንዛሪ ለማስገኘትና ለምስራቅ አፍሪካ የታዳሽ ኢነርጂ ማዕከል ለማድረግ ከፍተኛ ጥረት በማደረግ ላይ ነው፡፡  በቅርቡም የኤሌክትሪክ  ሀይል በመሸጥ የተጀመረ ሲሆን በቀጣይም ለሱዳንና ኬንያ በማቅረብ በምስራቅ አፍሪካ አስተማማኝ የሀይል ማዕከል የማድረግ ተግባሮች ይከናወናሉ፡፡