የአገልግሎት ገለፃ

 • ይህ አገልግሎት በውሃ እና ኢነርጂ ዘርፍ የተዘጋጁ የጂግራፊያዊ (GIS and RS) መረጃዎችን ምርምር ወይም ጥናት ለሚያደርጉ አካላት በማዘጋጀት ለመስጠት የታለመ ነው፡፡

መሟላት የሚገባቸው ዶክመንቶች

 • የመረጃ ጠያቂና ሥምና አድራሻ
 • የመረጃ ጠያቂው መሥሪያ ቤት/ተቋም
 • መረጃ የተፈለገበት ምክንያት
 • መረጃው የሚሸፍነው አካባቢ በወረዳ/ዞን/ ክልል ወይም የተፋሰስ አካባቢ ወይም ልዩ ቦታ ሥም
 • የተፈለገው የመረጃ ዓይነት ለምሣሌ የውሃ፣ የአፈር፣ የመሬት፣ ሽፋን፣ ወንዞች ክልል ወዘተ
 • መረጃው የሚፈለግበት ጊዜ
 • የመሥሪያ ቤት/ተቋም የድጋፍ ደብዳቤ

የአገልግሎት አሰጣጥ ሂደቶች

 • ከላይ የተመለከተውን ጥያቄ ተጠቃሚው ሞልቶ ሲያቀርብ የሚገኙ መረጃዎችን በማረጋገጥ ለማዘጋጀት የሚያስፈልገውን ጊዜ ማሳወቅ
 • መረጃው አነስተኛ መጠን ያለው ከሆነ በቀጥታ ይላክለታል ብዙ ከሆነ ግን በአካል መጥቶ እንዲወስድ ጊዜውና ሰዓቱ ይገለፅለታል
 • ተጠቃሚው መረጃውን ያገኛል