የባዮ ፊውል ልማት

ኢትዮጵያ ለባዮ ፊውል ልማት የሚውል ከ 23 ሚሊዮን ሄክታር በላይ ምቹ መሬት ያላት ሲሆን  እ.ኤ.አ 2007 ባዮ ፊውል ልማት ስትራቴጂ ተቀርፆ ተግባራዊ እንቅስቃሴ  ተጀመረ፡፡ ይህንን ምቹ ሁኔታ በመመስረት በርካታ የሀገር ውስጥና የውጭ ባለሀብቶች በዘርፉ ተሰማርተዋል፡፡ እስከ 2002 ዓ.ም ድረስ ከ 83 በላይ በለሀብቶች በዘረፉ ለመሰማራት ፍቃድ አውጥተዋል፡፡ ከ 183000 ሄክታር በላይ መሬት ሊለማ ችሏል፡፡

በአሁኑ ወቅት 10% ኢታኖል ከቤንዚን ጋር በመቀላቀል ለተሸከርካሪዎች አገልግሎት በመዋል ላይ ይገኛል፡፡ በሚቀጥሉት አምስት አመታት 196.9 ሚሊዮን ሊትር ባዮ ኢታኖልና 1.6 ሚሊዮን ሊተር ባዮ ዲዝል የማምረት ስራ እንዲሁም ባዮኢታኖልና ፊውልንና ባዮ ዲዝልን ከቤንዚንና ናፍጣ ጋር መቀየጫዎችን የማስፋፋት ስራዎች ይከናወናሉ፡፡