የሀይድሮ ፓወር ልማት

ሀገራችን ከፍተኛ የውሃ ሀይል እምቅ ሀብት አላት፡፡ ይህንን የውሃ ሃብት ከንፁህ መጠጥ ውሃ እና መስኖ ልማት ባሻገር ለኤሌክትሪክ ሀይል ልማት ለማዋል ጥረት በመደረግ ላይ ይገኛል፡፡ በየጊዜው እያደገ የሚሄደውን የኃይል ፍላጐት መሸከም የሚችል አስተማማኝ የሀይል አቅርቦት መኖር ወሳኝ በመሆኑና የውሃ ሀይል ከሌሎች የሀይል ምንጮች የበለጠ ሀገራዊ ፋይዳው የጐላ በመሆኑ መንግስት ለዘርፉ ከፍተኛ ትኩረት ሰጥቶት በመንቀሣቀስ ላይ ይገኛል፡፡

ከ1984 በፊት የነበረው የሀይል ማመንጫ ግንባታ ዝቅተኛ ሽፋን የነበረው ሲሆን ለዘርፉ የተሠጠውም ትኩረት እንቅስቃሴ እጅግ አነስተኛ ነበር፡፡ አጠቃላይ የሚመነጨው ኃይል 401.44 ሜጋ ዋት ያልበለጠ ነበር፡፡