ባዮፊውል ልማት

ሀገራችን 23 ሚሊዮን ሄክታር የሚሸፍን ለባዮፊውል (ባዮ-ኢታኖልና ባዮዲዝል) ልማት ምቹ የሆነ መሬት አላት የምግብ ዋስትናን በማይሻማ መልኩ በአግባቡ ለምቶ ከውጭ የምናስመጣውን ነዳጅ በመተካትና ለውጭ ገበያ በመቅረብ እንደዚሁም ለህብረተሰቡ ሰፊ የስ መስክ የሚፈጥርና ኑሮውን ለማሻሻል ከፍተኛ እገዛ ማድረግ የሚችል የልማት ዘርፍ ነው፡፡

በአጠቃላይ እስከ የእድገትና ትራንስፎርሜሽን እቅድ ዘመን ሁለት ዓመት ተኩል ድረስ በ6 ክልሎች በኦሮሚያ፣ ትግራይ፣ ደቡብ፣ አማራ፣ ቤንሻንጉል ጉምዝ፣ ሱማሌ፣ 2,534,798.7 ሄክታር መሬት በባዮዲዝል ተክሎች/ጃትሮፋ፣ ካስተር ወዘተ. በማልማት ያለና የሚለማ መሬት ተለይተዋል፡፡

በአማራ ግብራና ምርምር ኢንስቲትዩት ከተለያዩ ቦታ ከተወሰዱ የጃትሮፋ የዘር ምንጮች በተደረገው ጥናት መኤሶ 34.2% የዘይት መጠን እና 5.07 ቶን በሄክታር ምርት እና አሶሳ 37.4% የዘይት መጠን እና 3.76 ቶን በሄክታር ምርት ከተጠኑት 4 ዝርያዎች ውስጥ መኤሶ በምርት መጠንና አሶላ በዘይት መጠን የተሻሉ መሆናቸው ተረጋግጧል፡፡

የአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን ከአማራ መልሶ ማቋቋም ልማት ድርጅት ጋር በመሆን በአማራ ክልል ኦሮሚያ ዞን ባቲ ከተማ የሰራው 300 ሊትር አፍሪካ ፓወር ኢኒቬቲቭ በመቀሌ ከተማ 2000 ሊትር በቀን ማቀነባበር የሚችል የባዮዲዚል ማቀነባበሪያ ማሽን ተተክለዋል፡፡እንደዚሁም አትሪፍ ኦልተርኔቲቭ 3000 ሊጽር በቀን ማቀነባበር የሚችል የባዮዲዚል ማቀነባበሪያ ማሽን አስገብቶ በተከላ ሂደት ላይ ነው፡፡

የባዮ-ኢታኖል ቅይጥ መጠንን በተመለከተ በእድገትና ትራንስፎርሜሽን ሁለት አመት ተኩል ከመተሀራ ስኳር ፋብሪካ እና ከፊንጫአ ስኳር ፋብሪካ በድምሩ 31.88 ሚሊዮን ሊትር ለማምረት ታቅዶ 33.94 ሚሊዮን ሊትር ኢታኖል የተመረተ ሲሆን ከዚህ ውስጥ ኦይል ሊቢያ፣ ናይል ፔትሮሊየም እንዲሁም ናሽናል ኦይለ ኩባንያ በድምሩ 37 ሚሊዮን ሊትር ኢታኖል ከቤንዜል ጋር ተደባልቋል፡፡ በዚህም ወደ 26.74 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር በላይ የሚገመት የውጭ ምንዛሪ ማዳን ተችሏል፡፡

በዕድገትና ትራንስፎርሜሽን እቅድ ዘመን መጨረሻም (2007 ዓ.ም) 181.6 ሚሊዮን ሊትር በማምረት 64.38 ሚሊዮን ሊትር ከቤንዚን ጋር ሲቀየጥ ቀሪው በአገር ውስጥ ለምግብ ማብሰያነትና ለሌሎች አገልግሎቶች ይውላል፡፡