የውሃ ሀብት ልማት

የንፁህ መጠጥ ውሃ ልማት

በሀገራችን ባለፉት መንግስታት የንፁህ መጠጥ ውሃ አቅርቦት እጅግ አነስተኛ በመሆኑ የተነሳ ህብረተሰቡ ለከፋ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ችግሮች ሲጋለጥ ቆይቷል፡ ይህንን ችግር ለመቅረፍ መንግስት ከልማት አጋሮች ጋር በመሆን ባደረገው መጠነ ሰፊ እንቅስቃሴ ባለፉት ዓመታት አመርቂ ውጤት ተገኝቷል፡፡ በርካታ የመጠጥ ውሃ አቅርቦት ተቋማት በመገንባታቸው በከተማና በገጠር የሚኖር ህዝብ የአገልግሎቱ ተጠቃሚ ሆኗል፡፡ ከንፁህ ውሃ እጦት ጋር በተያያዘ ከሚከሰቱ የጤና ችግሮች ከመላቀቁ በላይ በውሃ ፍለጋ ይጠፋ የነበረውን ጊዜና ጉልበት በመቆጠብ ለልማት ለማዋል ተችሏል፡፡

ከ1984 ዓ.ም በፊት የንፁህ መጠጥ ውሃ አቅርቦት ሽፋን 20% በታች ነበር:: መንግስት ለዘርፉ በሰጠው ልዩ ትኩረት በ2002 ዓ.ም መጨረሻ የንፁህ መጠጥ ውኃ አቅርቦት ሽፋን በከተማ 91.5%  በገጠር 65.8 % እንዲሁም ሀገራዊ ሽፋኑ 68.5 % ሊደርስ የቻለ ሲሆን የአምስት ኣመቱ የእድገትና ትራንስፎርሜሽን እቅድ መተግበር በጀመረበት 2003 በጀት አመት  በገጠር  71.3   በከተማ  92.5  የደረሰ ሲሆን አጠቃላይ ሽፋኑም    73.3% ሊደርስ ችላል፡፡

የንጹህ መጠጥ ዉሃ ሽፋን የሚሰላዉ  በገጠርና በከተማ የሚኖረዉን ህዝብ ብዛት በመዉሰድ በገጠር  በ1.5ኪ.ሜ በከተማ በ0.5 ኪ.ሜ ክልል ዉስጥ በቀን በነፍስ ወከፍ በተከታታይ 15 እና 20 ሊትር  ለህብረተሰቡ ለማዳረስ በተቀመጥዉ አቅጣጫ መሰረት ነዉ::