ንፋስ ሀይል ልማት

በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች የንፋስ ሀይል በበቂ ሁኔታ ይገኛል፡፡ ጥናቶች እንደሚያመለክቱት በአማካኝ ከ 7 ሜ/ሰ በላይ የሆነ የንፋስ ፍጥነት እንዳለ ነው፡፡ይህንን ሀብት አለኝታ በመጠቀም የኤሌክትሪክ ሀይል ማመንጨት ወይም በቀጥታ መካኒካል ኢነርጂውን በማጎልበት ውሃን ለመሳብና ለመስኖ ስራ እንዲውል በማድረግ  የግብርናውን ዘርፍ ለማገዝ ያስችላል፡፡ በአሁኑ ወቅት በመገንባት ላይ ያሉት በትግራይ ክልል  አሸጎዳ የንፋስ ሀይል ማመንጪያ 120 ሜጋ ዋትና የአዳማ I የንፋስ  ሀይል ማመንጪያ 51 ሜጋ ዋት ይጠቀሳሉ፡፡
ተ.ቁ የሚከናወኑ ተግባራት መለኪያ እስከ 2002 ዓ.ም. የተከናወነ ከ2003 እስከ 2007 የሚከናወን
1 በንፋስ ኢነርጂ የሚሰሩ የኤሌክትሪክ ማመንጫዎችን ማሰራጨት በቁጥር 0 10
2 በንፋስ ኢነርጂ የሚሰሩ የውሃ መሳቢያ ቴክኖሎጂዎችን ማሰራጨት በቁጥር 25 1000