የፀሀይ ሀይል ልማት

የኢትዮጵያ ጂኦግራፊያዊ አቀማመጥ በምድር ወገብ አካባቢ እንደመሆኑ ከፍተኛ የሆነ የፀሀይ ኢነርጂ ሀብት እንድትታደል አድርጓታል፡፤ በሀገራችን 5.20 KWh የፀሀይ ሀብት በሜትር ካሬ ቦታ ላይ በቀን ማግኘት ይቻላል፡፡ ይህንን ሀብት በመጠቀም ከዋናው የኤሌክትሪክ መስመር ርቀው የሚገኙ የገጠር ቤተሰቦች፣ የጤና ኬላዎችና ት/ቤቶች ተጠቃሚ ማድረግ ይቻላል፡፡ ከቤት ውስጥ ፍጆታ ባሻገር የኢንፎርሜሽን ኮሙንኬሽን ቴክኖሎጂን በገጠር አካባቢዎች በማስፋፋት ልማቱን ለማፋጠን ይረዳል፡፡ በዚህም መሰረት፡-

ተ.ቁ የሚከናወኑ ተግባራት መለኪያ እስከ 2002 ዓ.ም. የተከናወነ ከ2003 እስከ 2007 የሚከናወን
1 ለቤተሰብ የሚሆኑና በፀሃይ ኢነርጂ የሚሰሩ የኤሌክትሪክ ማመንጫዎችን ማሰራጨት በቁጥር 5000 150000
2 ለተቋም የሚሆኑና በፀሃይ ኢነርጂ የሚሰሩ የኤሌክትሪክ ማመንጫዎችን ማሰራጨት በቁጥር 500 3000
3 በፀሃይ ሀይል የሚሰሩ የውሃ ማሞቂያዎን ማሰራጨት በቁጥር 0 1500
4 የፀሃይ ቴክኖሎጄ ማሰልጠኛ ማቋቋም በቁጥር 0 1